Saturday, October 26, 2013

የህዋሃት ጀነራል መኮንኖች በሃብት ብዛት እየተመፃደቁ ነው!!!


                                             ጄ/ል ሞላ ሃ/ማሪያም
የጀነራል መኮንኖች የምደባ ለውጥ ተካሄደ !
ሜጀር ጀነራል አደም መሀመድ የአየር ሀይል አዛዥ ሆነው መሾማቸውንና የአዛዥ ጄነራሎች ላይም የምደባ ለውጥ መደረጉን ፡፡ በአየር ሀይል አዛዥ በነበሩት ሜጀር ጀነራል ሞላ ሀይለማርያም ምትክ የተሾሙት ሜጀር ጀነራል አደም መሀመድ  አቢዬ ግዛት የሠላም አስከባሪ ሀይል ምክትል አዛዥነት ያገለገሉ እንዲሁም የመከላከያ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ነበሩ፡፡
በሌሎች የመከላከያ የስራ ምድብ ቦታዎች ላይ የአዛዦች የምደባ ለውጥ መደረጉን የተናገሩት ምንጮች፣ አዲስ የሀላፊነት ምደባ ከተሠጣቸው ውስጥ ሌተናል ጀነራል ሠአረ መኮንን፣ ሌተናል ጀነራል አበባው፣ ሜጀር ጀነራል ዮሀንስ ወልደጊዮርጊስ፣ ሜጀር ጀነራል ገብራት አየለ እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
የህዋሃት ጀነራል መኮንኖች በሃብት ብዛት እየተመፃደቁ ነው!
Ethiopian generals, who for the vast majority are Tigrayan, have a good many material advantages, such as free petrol (gasoline), an official car, free electricity and water, to name but a few. However, in some cases, these advantages can go even further, such as the possibility to import domestic equipment financed by the ministry for defence. They have also benefited from plots of land in the Bole neighbourhood in Addis Ababa and some of these generals were attributed official housing during the time when the late Meles Zenawi was Prime Minister. Some of them, like General Tadesse Gawna and Colonel Tsehaye Manjus, had no qualms about selling the plots of land they had been attributed. Others rent their official dwellings to third parties. One who does precisely this is General Gezae Abera who headed the army logistics department before going to live (asylum) in Sweden. Others are Generals Gebre Egziabher Mebratu, Teklai Ashebir and Fisseha Kidane, who receive monthly rents of between 30 and 40,000 birrs (€1100 to €1500) each.

Monday, October 21, 2013

Call for a Peaceful Rally in Bergen, Norway!



A statement from the Organizing Committee of the peaceful rally.

We, members of the Oromo community residing in Bergen, Norway, neighboring communities and friends of Oromo, are very concerned about human rights violations particularly against the Oromo in Ethiopia. Therefore, we have a plan to have a peaceful rally against the dictatorial regime in Ethiopia on October 25, 2013.

Time and Place:
The demonstration will be held on the 25th October 2013 from 13.00 to 15.00. We will gather at the Blue Stone, and we will head through the gallery, pass along the exhibition center and move all the way to the police station and, there, deliver a letter to the person in charge.

Aims:


• We shall demonstrate against human rights violations by the dictatorial regime in Ethiopia. We will turn to the new Norwegian government to press the Ethiopian government to respect human rights and release all political prisoners.

• Call for the release of Bekele Gerba, Mesfin Abebe and other political prisoners in Ethiopia.

• Candlelight vigil to remember the Oromo activist Engineer Tesfahun Chamada, who died in the Kaliti Prison after a horrible and inhuman torture by the Ethiopian government. And victims of the Kofalee Massacre of August 2013.

All protesters are welcome to join us to stand against, and say ‘no’ to the dictatorial and tyranny government.

Regards,

Dandana Bafkane,
Dejene Sorry,
Members of the Committee

For Further information, contact: Abdi Gameda Chali (Tel. +4794724502)

የወያኔ ቀጣይ የፖለቲካ ሴራዎች?

የወያኔ ቀጣይ የፖለቲካ ሴራዎች

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

እንደ መንደርደሪያ
የሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ-ምህረት የመጀመሪያ ወር ተጠናቅቋል፤ አዳዲስ ክስተቶችም ታይተዋል፤ ያለፉት አስራ ሁለት
ዓመታትንበጃንሆይ ቤተ-መንግስት ያሳለፉት ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፣ በኦህዴዱ ሙላቱ ተሾመ መተካታቸው አንዱ
ነው፡፡ አባይ ፀሀዬና ዶ/ር ካሱ ኢላላም ከበረከት ስምዖንና ኩማ ደመቅሳ በተጨማሪ በሚኒስትር ማዕረግ የኃ/ማሪያም ደሳለኝ
‹‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር›› አማካሪ ሆነው መሾማቸው ሌላው ነው (በነገራችን ላይ ሹመቱን እንደተለመደው አይቶ ችላ ብሎ
ለማለፍ የማያስችሉ ሶስት ምክንያቶች አሉ፤ የመጀመሪያው በሀገሪቱ ለአንድ የሥራ መደብ አራት ሚንስትር ተሹሞ አለማወቁ
ሲሆን፤ ሌላው ተሿሚዎቹ፣ ኢህአዴግን ከመሰረቱት አራት ፓርቲዎች በኮታ የተወጣጡ መሆናቸው ነው፡፡ ሳልሳዊውና
አስገራሚው ደግሞ ሰዎቹ ፖለቲከኞች እንጂ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ምሁራን አለመሆናቸው ነው)
እነዚህ ሁሉ በግልፅ የሚታወቁ የዓመቱ መጀመሪያ ክስተቶች ናቸው፡፡ ለስርዓቱ ቅርበት ካላቸው ምንጮቼ ባገኘሁት መረጃ
መሠረት፣ በቅርቡ ‹ሚዲያ›ን እና ‹የይቅርታ ስነስርዓት›ን የተመለከቱ አዳዲስ አዋጆች በተወካዮች ም/ቤት ለመፅደቅ
ተዘጋጅተዋል፡፡ በተለይም ‹ሚዲያው›ን የሚመለከተው አዲሱ ህግ፣ ከአምስት ዓመት በፊት ተግባር ላይ የዋለውን የ‹‹ፕሬስ
አዋጁ››ን የአፋና ጉልበት ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ፣ የነበረው አንፃራዊ ጭላንጭል ጭራሽ ሊዳፈን እንደሚችል መረጃዎች
ያሳያሉ፡፡ ‹‹የይቅርታ አዋጁ››ም ቢሆን ጥቂት የአገዛዙ ጉምቱ ባለስልጣናት ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ የአመራር አባላትና አንዳንድ
የግል ጋዜጠኞች ብንታሰርም በይቅርታ እንፈታለን በሚል ግንባሩን እየተፈታተኑ ነው›› ሲሉ ደጋግመው መደመጣቸውን፣
ከአዲሱ ‹‹የይቅርታ አሰጣጥ እና አፈፃፀም ሥነ-ሥርአት አዋጅ›› ጋር ካያያዝነው፣ አንቀፆቹ ሊኖራቸው የሚችለውን አንድምታ
መገመቱ ብዙ ከባድ አይሆንም፡፡
ለማንኛውም ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጉልበታም በመሆን ቀጣዩን ምርጫ በስኬት ለማለፍ፣ በያዝነው ዓመት የተለያዩ
አፋኝ ህጎችን በማውጣት ፓርቲዎቹን የማዳከም ስራ ለመስራት በተለየ መልኩ መዘጋጀቱ ተሰምቷል፡፡ በአናቱም ኃ/ማርያም
ደሳለኝ-ከመንግስት፣ ከፓርቲውና ከውስን የግል ጋዜጠኞች፤ ደመቀ መኮንን-ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ፤ ሽመልስ ከማል -ከኢዜአ ጋር
ያደረጓቸው ቃለ-መጠይቆችም ይህንን መረጃ የሚያጠናክር ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የዚህ ፅሁፍ ተጠየቅም አገዛዙ በቀጣይ ሊኖረው
የሚችለውን ባህሪ እና ‹አምስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ›ን አስቀድሞ ለማሸነፍ እየቀመረ ያለውን ሴራ መጠቆም ነው፡፡

Friday, October 18, 2013

Political prisoners tortured in Ethiopia



Political prisoners tortured in Ethiopia



Addis Ababa : Political prisoners in Ethiopia held under inhumane conditions and tortured regularly, says Human Rights Watch

In a report that Human Rights Watch publishes, based on 35 interviews, says former prisoners Maekelawi prison in the capital Addis Ababa that they were beaten, kicked and beaten with sticks and rifle butts during interrogation.

Others say that they were hung by the wrist in painful positions for hours while they were beaten.




Ethiopian authorities rejected the report as a lie. Government spokesman Shimeles Kemal says it is one-sided, ideologically colored and that the missing evidence.




According to HRW, most sitting in the previously unknown Maekelawi prison political prisoners, who are to receive visits by lawyers or relatives.

HRW accused the Ethiopian authorities to use anti-terror laws to remain silent in death political opponents and journalists.

Tuesday, October 15, 2013

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰልፍ ክልከላ ቀጭን መስመር

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰልፍ ክልከላ ቀጭን መስመር?



ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መስከረም 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ለሁለተኛ ጊዜ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡


በበርካታ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሰልፍ የማድረግ ሕገ መንግሥታዊ መብት ዙሪያ የሰጡት ምላሽ ግን አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ኤልሳቤጥ እቁባይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረበችው ጥያቄ የሚከተለው ነበር፡- ‹‹የትግል እንቅስቃሴአቸውን አገር ውስጥ እያደረጉ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ ጊዜዎች በተለያዩ ከተማዎች ከመንግሥት ምላሽ ይፈልጋሉ ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ሰላማዊ ሰልፎችን አድርገዋል፡፡ ምንም እንኳን ሰልፎቹን አስመልክቶ በመንግሥት ኮሚኒኬሽን በኩል የተሰጡ መግለጫዎች ቢኖሩም ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከቀረቡ ጥያቄዎች ‹ምላሽ ያሻቸዋል፣ አግባብነት አላቸው› ብለው መንግስትም በተለያየ መንገድ ከሚሰበስባቸው መረጃዎች የወሰዷቸው ጥያቄዎች አሉ ወይ››

ለጥያቄው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው ምላሽ ለብዙዎች የሚያረካ ነበር ለማለት ያስቸግራል፡፡ ይልቁንም ምላሹ ሌሎች ተጨማሪ በርካታ ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡ በመልሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ሕገ መንግሥታዊ መብት መሆኑን፣ መንግሥታቸው በጫና ሐሳቡን የሚቀይር እንዳልሆነ፣ ተመሳሳይ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ከተጠየቁ መንግሥት አንድ ቦታ ላይ እንደሚያቆመው፣ የፓርቲዎች መብዛት ሰልፉን እንዳበዛው፣ ሰልፉ የሚታወቀው ውጭ ባሉ የእቅዱ ባለቤቶች እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

Saturday, October 5, 2013

ቀጣዩ የኢሕአዴግ ዒላማ ማኅበረ ቅዱሳን ይኾን?

ቀጣዩ የኢሕአዴግ ዒላማ ማኅበረ ቅዱሳን ይኾን?


(ፋክት መጽሔት፤ ቁጥር 14 መስከረም ፳፻፮ ዓ.ም.)






ተመስገን ደሳለኝ

የኢሕአዴግ ታጋዮች የመንግሥት ‹‹ጠንካራ ይዞታ›› የሚባሉ ከተሞችን ሳይቀር መቆጣጠር ችለዋል፤ ወደ አዲስ አበባም የሚያደርጉት ግሥጋሴም ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ሳይቀር ዕንቅልፍ ነስቷል፡፡ በአንዳች ተኣምር ግሥጋሴውን መግታት ካልቻሉ በጥቂት ወራት ውስጥ ሁሉም ነገር ታሪክ እንደሚኾን በማወቃቸው መላ በማፈላለጉ ላይ ተጠምደዋል፡፡ በዚህን ጊዜ ነበር(የሐሳቡ አመንጪ ተለይቶ ባይታወቅም)፣ ‹‹ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አጭር ሥልጠና ሰጥቶ ከሀገሪቱ ሠራዊት ጎን ማሰለፍና የ‹ወንበዴውን ጦር› ማድረሻ ማሳጣት›› የሚለው ሐሳብ እንደ መፍትሔ የተወሰደው፡፡

እናም መንግሥቱ ራሳቸው ተማሪዎቹን በዩኒቨርስቲ አዳራሽ ሰብስበው እንዲህ ሲሉ አፋጠጧቸው፡- ‹‹እነርሱ (ኢሕአዴግና ሻዕቢያን ማለታቸው ነው) ለእኵይ ዓላማቸው ከእረኛ እስከ ምሁር ሲያሰልፉ እናንተ ምንድን ነው የምትሠሩት? በሰላማዊ ሰልፍና በስብሰባ ብቻ መቃወም ወይስ ወንበዴዎቹ እንዳደረጉት ከአብዮታዊ ሠራዊታችነ ጎን ቆማችኹ የአገሪቱን ህልውና ታስከብራላችኹ?››

ይህን ጊዜም አስቀድሞ በተሰጣቸው መመሪያ ከተማሪው ጋራ ተመሳስለው በአዳራሹ የተገኙት የደኅንነት ሠራተኞችና የኢሠፓ ካድሬዎች ‹‹ዘምተን ከጠላት ጋራ መፋለም እንፈልጋለን›› ብለው በስሜትና በወኔ እየተናገሩ በሠሩት ‹ድራማ› ተማሪው ትምህርት አቋርጦ እንዲዘምት ተወሰነ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም ተዘጋ፤ ተማሪዎቹም ለወታደራዊ ሥልጠና ደቡብ ኢትዮጵያ ወደሚገኘው ብላቴ የአየር ወለድ ማሠልጠኛ ከተቱ፡፡

ከመላው ዘማቾች ዐሥራ ሁለት የሚኾኑ ተማሪዎች ተሰባስበው ሲያበቁ በየቀኑ ካምፓቸው አቅራቢያ ወደሚገኘው ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ከመዐቱ ይታደጋቸው ዘንድ ፈጣሪያቸውን በጸሎት መማጠን የሕይወታቸው አካል አደረጉት፤ ከቀናት በኋላም በአንዱ ዕለት አንድም ለመታሰቢያና ለበረከት. ሁለትም ስብስቡ ሳይበተን ወደፊት እንዲቀጥል በሚል ዕሳቤ ‹‹ማኅበረ ሚካኤል›› ብለው የሠየሙትን የጽዋ ማኅበር መሠረቱ፡፡ . . . ይኹንና ከመካከላቸው አንዳቸውም እንኳ በ፲፱፻፸፯ ዓ.ም በፓዌ መተከል ዞን የተደረገውን የመልሶ ማቋቋም ሠፈራ ፕሮግራም እንዲያመቻቹ በዘመቱ ተማሪዎች ከተመሠረተውና ከተለያዩ የጽዋ ማኅበራት ጋራ በመዋሐድ የዛሬውን ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› እንደሚፈጥሩ መገመት የሚችሉበት የነቢይነት ጸጋ አልነበራቸውም፤ የኾነው ግን እንዲያ ነበር፡፡



ማኅበረ ቅዱሳን

የ‹‹ማኅበረ ሚካኤል›› መሥራቾች ከተማሪ ጓደኞቻቸው ጋራ ‹‹ይለያል ዘንድሮ የወንበዴ ኑሮ››ን እየዘመሩ የገቡበት ወታደራዊ ሥልጠና ተጠናቅቆ ወደ ጦር ሜዳ ከመግባታቸው በፊት ዐማፅያኑ አሸንፈው የመንግሥት ለውጥ በመደረጉ ሥልጠናቸውን ሳይጨርሱ ወደየመጡበት ተመለሱ፡፡ ኾኖም ለውጡ በተካሄደ በዓመቱ እነርሱን ጨምሮ በአምላካቸው፣ በጻድቃን፣ በሰማዕታትና በመላእክታት ስም የተመሠረቱ[ከአቡነ ጎርጎርዮስ ዘንድ ሲማሩ የቆዩ] የተለያዩ ማኅበራት ተሰባስበው ወደ አንድ እንዲመጡ መደረጉ ሊጠቀስ የሚገባ ልዩነት ባይፈጥርም ስያሜው ግን ብርቱ ክርክር አሥነሳ፤ አቡነ ገብርኤልም ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ብዬዋለኹ›› ብለው ውጥረቱን አረገቡት፡፡ ዕለቱም[ልደቱን የሚቆጥርበት] ግንቦት ፪ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. እንደነበር ተጽፏል፡፡

ዓላማው ምንድን ነው?